የኢፌድሪ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራትና ኤጀንሲ

የኢፌድሪ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራትና ኤጀንሲ ደቡብ ወሎ ወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ከተማ በመገኘት በአሸባሪው ህወሀት ጉዳት ለደረሱባቸው ማህበረሰቦች ድጋፍ አደረጉ ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አንዷለም አድማሴ ዛሬ እዚህ ቢስቲማ ከተማ ላይ ተገኝተን በወቅታዊ ጦርነቱ ምክንያት ንብረታቸው የወደመባቸው ወንድሞቻቸውን እናቶቻቸውን ያጡ የተጎዱ ማህበረሰቦችን ለመደገፍ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ሰራተኞችና ተቋሙ በመተባበር ያቅማችንን ለመደገፍና አለናችሁ ለማለት ለህፃናት የተለያዩ አልሚ ምግብ የፅዳት መጠበቂያና አልባሳትን በአጠቃላይ ከ6 መቶ ሺ ብር በላይ ድጋፍ አድርገናል ብለዋል።

የወረባቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኻሊድ መሀመድ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ሰራተኞችና ተቋሙ ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው በአሁኑ ሰአት የሚመጣው ድጋፍ አናሳ ቢሆንም የሚመጣን ድጋፍ ከወረዳው ምግብ ዋስትና ጋር በመነጋገር ቅድሚያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የህብረተሰባችን ክፍል እንዲደርስ እያደረግን እንገኛለን ብለዋል።