ለህገ ወጥ የትምህርት ማስረጃዎች ጉዳይ ተጠያቂው ማነው?

በመቶ ሺህ ለሚቆጠሩት ህገ ወጥ የዲግሪና ማስተርስ የትምህርት ማስረጃዎች ጉዳይ ተጠያቂው ማነው? ማንኛውም ሰው ሊያዳምጠው የሚገባ ውይይት፤ ፋና ቴሌቪዥን ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ ጋር ያደረገውን ውይይት አዘጋጅቶ ለህዝብ ተደራሽ አድርጓል። ለትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የጥራት መጓል የሚቆጨው ዜጋ ሁሉ ይህን ውይይት አዳምጦ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የተሻለ ግንዛቤ እንድንይዝ ይረዳናል።

በዘርፉ ካለፉት 20 ዓመታት ጀምሮ የተከማቹ ችግሮችን እውነታውን ተረድቶ የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የሚፈልጉ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ አመራሮች እና አጠቃላይ ዜጎች በቅንነት ውይይቱን አዳምጠው ባለሥልጣኑ ለመቅረፍ የተያያዘውን የለውጥ ሂደት ለመደገፍ ከጎኑ እንዲቆሙ ይህን ቪዲዮ ለመጋበዝ እንወዳለን።