የጤና ፕሮግራሞች የእውቅና አሰጣጥ መመሪያና ስታንዳርድ

በጤና ሙያ ተመርቀው ካጠናቀቁ በኋላ የብቃት መመዘኛ ሲፈተኑ ማለፉ የማይችሉ ምሩቃን መኖራቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ ትክክለኛ እውቅና በሌላቸው ተቋማት ላይ ስለሚማሩ ነው። ምክክሩ እውቅና ለመስጠትና ለመከልከል የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ጤና ማህበር ፕሬዚዳንት ዶክተር ተግባር ይግዛው በበኩላቸው ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት ጥራት ያለው ትምህርት ጥራት ባለው የጤና ተቋም መማር ሲቻል ነው። ጥራት ከሌለው የጤና የትምህርት ተቋም ጥራት ያለው ትምህርት ማግኘት አይቻልም። ስለዚህ የትምህት ጥራት ለማረጋገጥ ጠንካራ የትምህርት አተገባበር ስርአት መመስረት አለበት ብለዋል። ለአላማው ስኬት የሙያ ማህበሩ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ጋር ለመስራት ቁርጠኛ ሆኖ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

የመግባቢያ ሰነዱ ተዘጋጅተው በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የሚሰራጩ የትምህርት ተቋማት ማስታወቂያዎች ህጋዊነታቸውን እና ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የሚያግዝ እንደሆነ ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ ገልጸዋል፡፡ የትምህርት ተቋማትን በተመለከተ ህዝቡን የሚያሳስቱ ማስታወቂያዎችን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ለአብነት ያህል፡- “ሙሉ እውቅና ያለው” በሚል ማስታወቂያ ማስነገር ትክክል አይደለም፤ “ሙሉ እውቅና አለኝ” ብሎ ራሱን የሚያስተዋውቅ ተቋም “የሌላኛው ተቋም የእውቅና ፈቃድ ሙሉ አይደለም” የሚል ትርጉም ይኖረዋል፤ የእውቅና ሙሉ የእውና ፈቃድ ተብሎ የሚሰጥ ፈቃድ እንደሌለ ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም ህዝብን ያሳስታል፤ ለአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ወይም በኢኮኖሚክስ የእውቅና ተሰጥቶታል ካለ፤ የተሰጠው በየትኛው ካምስ እንደሆነ መግለጽን ይፈልጋል፣ የምንሰጠው የእውቅና ፈቃድ በጊዜ እና በቦታ የተገደበ ነው፤ የትምህርትና ስልጠና ተቋማትን ማስታወቂያ አዘጋጅተው የሚያሰራጩ የማስታወቂያና የሚዲያ ድርጅቶች ይህን መሰረት አድርገው መስራት አለባቸው፤ ከዚህ አንጻር ሁለቱ ባለስልጣን መ/ቤቶች የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ የትምህርት ማስታወቂያዎች ህጋዊነታቸው ተጠብቆ በጥራት እንዲሰራጩ ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ኮሌጅ ዲን፣ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች፣ ሌሎች የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የጤ ሙያ ማህበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል።